የጥሞና ቃል ክፍል 4

መዝ. 119፥97-105

“አቤቱ፥ ሕግህን እንደ ምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።

ለዘላለም ለእኔ ነውና ትእዛዝህ ከጠላቶቼ ይልቅ አስተዋይ አደረገኝ።

ምስክርህ ትዝታዬ ነውና ካስተማሩኝ ሁሉ ይልቅ አስተዋልሁ።

ትእዛዝህን ፈልጌአለሁና ከሽማግሌዎች ይልቅ አስተዋልሁ።

ቃልህን እጠብቅ ዘንድ ከክፉ መንገድ ሁሉ እግሬን ከለከልሁ።

አስተምረኸኛልና ከፍርድህ አልራቅሁም።

ቃልህ ለጕሮሮዬ ጣፋጭ ነው ከማርና ከወለላ ይልቅ ለአፌ ጣፈጠኝ።

ከትእዛዝህ የተነሣ አስተዋልሁ ስለዚህ የሐሰትን መንገድ ጠላሁ።

ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው።

መዝሙረ ዳዊት ሲጀምር “ . . . ሕጉንም በቀንና በሌሊት ያስባል” (1፥2) ይላል። በዚህም ክፍል “ቀኑን ሁሉ እርሱ (ቃልህ) ትዝታዬ ሆነ” ይላል። ይህ በዘመናችን አባባል ሜዲቴሽን ይባላል፣ የእግዚአብሔርን ቃል ቀኑን ሁሉ ማሰላሰል! ቶማስ ካምፕስ የተባለ ሰው ስለዚህ ሀሳብ ሲናገር “a familiar friendship with Jesus” ይለዋል [Thomas a Kempis The Imitation of Christ, (Garden City, NY: Image, 1955), 85] ። ቀኑን ሙሉ ቃሉን ማሰላሰል ወይም መዲቴት ማድረግ ማለት በማያቋርጥ የእግዚአብሔር መገኘት (አብሮነት – Presence) መሆን ማለት ነው። በመዲቴሽን ልምምድ ውስጥ መሆን ማለት ከውስጥ ማንነታችን ክርስቶስን ለማምለክ፣ ለእርሱ የነፍሳችን መሥዋዕት ለማቅረብና ለእርሱ ህልውና በውስጣችን መቅደስ ማመቻቸት ማለት ነው። በዚህ ዓመት ይህንን መንፈሳዊ ልምምድ እናሳድግ!

“በመንፈሱ በውስጥ ሰውነታችሁ በኃይል እንድትጠነክሩ ክርስቶስም በልባችሁ በእምነት እንዲኖር

እንደ ክብሩ ባለ ጠግነት መጠን ይስጣችሁ፤ የእናንተ ሥርና መሠረት በፍቅር ይጸና ዘንድ” ኤፌ. 3፥16-17

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *