The Ethiopia Evangelical Church in Toronto (EECT) praises actions taken by the federal government of Ethiopia, the various levels of local governments, the religious and community organizations and individuals to reduce the spread of COVID-19 in Ethiopia. The EECT responds to the urgent rescue request by the Ethiopian people by donating $50,000 (Fifty Thousand) Canadian dollar that can be used to fight spread of Covid-19.
This aid will be sent to Ethiopia through Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Canada along with fund collected from other members of the Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Canada. Reports will be provided to the members of the church. It is our prayer that God intervenes in the spreading of Covid-19 and heals who are infected.
Much love in Christ,
The Board of Ethiopia Evangelical Church in Toronto
በቶሮንቶ የምትገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን (Ethiopia Evangelical Church in Toronto) በኢትዮጵያ የ COVID-19 ስርጭትን ለመቀነስ በኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት ፣ በየአከባቢው ያሉ ክልላዊ አስተዳደሮች፣ የሃይማኖት እና የህብረተሰብ ድርጅቶች እና ግለሰቦች እየወሰዱ ያሉትን እርምጃዎች ሁሉ አድንቃለች፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ አስቸኳይ የማዳን ጥሪ ምላሽ ለመስጠት በቶሮንቶ የምትገኘው የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የCovid-19 ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚውል የ$50,000 (ሃምሳ ሺ) የካናዳ ዶላር እርዳታ ለግሳለች።
ይህ እርዳታ ሌሎች በካናዳ ያሉ የኢትዮጵያ ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ህብረት (Ethiopian Evangelical Churches Fellowship in Canada) አባላት እያሰባሰቡት ካለው እርዳታ ተጨምሮ በሕብረቱ በኩል ወደ ኢትዮጵያ ፈጥኖ ይላካል። ውጤቱን ለምዕመናን ሁሉ ወደፊት ይገለጻል። እግዚአብሄር የCovid-19 ስርጭትን ገደብ እንዲያበጅለትና ለታመሙትም ፈውስን እንዲሰጣቸው ጸሎታችን ነው::
በብዛው የክርስቶስ ፍቅር
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ቦርድ