eectmedia

eectmedia

የጥሞና ቃል ክፍል 40

“እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ” (ዮሐ. 17፥4) ይህንን ቃል ሳነበው እጅግ አስገረመኝ። ጌታ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ሁለት ነገሮችን እንዳደረገ ያሳያል። 1ኛ እግዚአብሔር አብ የሰጠውን ሥራ “ፈጸምኩ” ይላል። 2ኛው “አከበርኩህ” ይላል። በሕይወታችን ዘመን እግዚአብሔር የሰጠን ሥራዎች አሉ። በእርግጥ ደህንነታችን የተመሠረተው…

የጥሞና ቃል ክፍል 39

“በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል” (1ጴጥ. 5፥10) በዚህ ቃል ውስጥ እግዚአብሔር ወደ ዘላለም ክብሩ እንደጠራን፣ የዚህ የመጠራታችን ዋና መሠረትም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ እንመለከታለን። ሌላው እውነት…

የጥሞና ቃል ክፍል 38

“ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል መጣለት። ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፥ ያደረገው እግዚአብሔር፥ ያጸናውም ዘንድ የሠራው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ” (ኤር. 33፥1-3) በመጀመሪያ ኤርምያስ…

የጥሞና ቃል ክፍል 37

የሚጠራችሁ የታመነ ነው፣ እርሱም ያደርገዋል!” ( 1ተሰ. 5፥24) ጌታ በብዙ ነገር ለኛ ታማኝ ሆኖ ይኸው እስከዛሬ ቆመናል። ከእግዚአብሔር ጋር የተራመዱ ታላላቅ የእግዚአብሔር ባርያዎችም ይህ ታማኝነቱ እጅግ እያስገረማቸውና እያስደነቃቸው አልፈዋል። የእግዚአብሔር ባርያ ሙሴ ባሕርያተ እግዚአብሔርን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል! “እርሱ አምላክ ነው፣…

የጥሞና ቃል ክፍል 36

“ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃል እየሰሙ ሲያስጠብቡት ሳሉ፥ እርሱ ራሱ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ነበር፤ በባሕር ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ግን ከእነርሱ ውስጥ ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደ ነበረች ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት…

የጥሞና ቃል ክፍል 35

“አቤቱ፥ በሕዝብም ፊት በወጣህ ጊዜ፥ በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥ ምድር ተናወጠች፣ ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠበጠቡ” (መዝ. 68፥7-8) እግዚአብሔር በሕዝቡ ፊት ሲወጣ የሚሆኑ ነገሮች እንመለከታለን። በተራራ ይሁን በሸለቆ የእግዚአብሔር ሕዝብ በሚገኝበት ሁኔታ ሁሉ እግዚአብሔር ይወጣል። ለምን ይወጣል?…

በግምባራቸው ወደቁ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው | የማለዳ ጥሞና

ሁለት ሚልዮን የሚያህል ሕዝብ በውኃ ጥም ሲያጉረመርም መሪዎች ምን ማድረግ ይቻላሉ? ምንስ ማለት ይችላሉ? የምድረ በዳ ጉዞ እምነትን የሚፈትን ጉዞ ነው፣ አማኝ የሚናወጥበትና የሚበጠርበት ጉዞ ነው። ሰው በምድረ በዳ ሲያልፍ እንኳን በመሪዎች ላይ በእግዚአብሔር በራሱም ላይ እንኳ ብዙ መናገር የሚቃጣበት…

የጥሞና ቃል ክፍል 33

“ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ” ኢያሱ 3፥1 ዮርዳኖስን ለመሻገር የሚዘጋጅ ሰው ማልዶ መነሳት አለበት። ይህ ደግሞ የጸሎት ሕይወታችንን ያሳያል። የሚጸልይ ሰው ይሻገራል። የጸሎት ሰው በምንም ዓይነት መከራ ውስጥ ቢያልፍም ይሻገራል።…

የጥሞና ቃል ክፍል 32

 “ነገር ግን . . .” “የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ ደግሞም ጽኑዕ ኃያል ነበረ፥ ነገር ግን ለምጻም ነበረ” (2ነሥ. 5፥1) በእያንዳንዱ ሰው ሕይወት “ነገር ግን” የሚባል አሉታዊ…