የህንፃ ተንከባካቢና ፅዳት (Caretaker)
Website Ethiopian Evangelical Church in Toronto
የሥራ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በቶሮንቶ
የህንፃ ተንከባካቢና ፅዳት (Caretaker)
የሥራው ዓይነት
የህንፃ ተንከባካቢና ፅዳት (Caretaker)
የሥራ ሰዓት
በሳምንት 30 ሰዓት
ተጠሪነቱ
ለህንፃ ስነውበት ጥበቃ ክፍል
ዋና ዋና ኃላፊነቶች
ፅዳትና ዝግጅት
- የቤተክርስቲያኑን ዋና አዳራሽ፣ ቢሮዎች፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ የመጸዳጃ ክፍሎችና ኮሪደሮችን በየቀኑ/በየሳምንቱ በተዘጋጀው ፕሮግራም መሰረት በጥራት ማፅዳትና ማስተካከል።
- ወለሎችን መወልወልና በቫክዩም (Vacuum) ማፅዳት፣ ማጠብና ማጣራት።
- የቆሻሻ ባልዲዎችን በወቅቱ ባዶ ማድረግና ቆሻሻዎችን ማስወገድ።
- ለመንፈሳዊ አገልግሎቶችና ለተለያዩ ፕሮግራሞች የቦታ ዝግጅት ማድረግ (ወንበሮችን፣ ጠረጴዛዎችንና መድረክን ማስተካከል)።
አነስተኛ የህንፃ ጥገና ስራዎች (Minor Maintenance)
- የህንፃውን አጠቃላይ ሁኔታ መከታተልና አነስተኛ ጥገናዎችን (ለምሳሌ፡ አምፖል መቀየር፣ ቀላል የውሃና የመጸዳጃ ቤት ጥገናዎች፣ በሮችና እቃዎች ላይ ያሉ ቀላል ብልሽቶችን ማስተካከል) ማከናወን።
- ትልልቅ ጥገናዎች ወይም የባለሙያ እርዳታ የሚሹ ጉዳዮች ሲኖሩ ለህንፃ አስተዳደር ክፍል በወቅቱ ሪፖርት ማድረግ።
ደህንነትና ቁጥጥር
- የፅዳት እቃዎችንና ኬሚካሎችን በጥንቃቄ መያዝ፣ መጠቀምና በስርአት ማስቀመጥ።
- አገልግሎት ሲጠናቀቅ በሮች፣ መስኮቶችና የመብራት/የማሞቂያ ስርአቶች በትክክል መዘጋታቸውን ማረጋገጥ።
ተፈላጊ መስፈርቶችና ብቃቶች
- በፅዳትና በህንፃ ተንከባካቢነት (Caretaker/Janitor) ስራ ላይ የቀደመ ልምድ ያለው።
- አነስተኛ የቤትና የህንፃ ጥገና ስራዎችን የማከናወን ተግባራዊ ችሎታ ያለው።
- ስራን በግል ተነሳሽነትና ያለብዙ ቁጥጥር በጥራት ማከናወን የሚችል።
- በቡድንና ከቤተክርስቲያኑ አመራሮችና አገልጋዮች ጋር በመከባበርና በጥሩ ስነ-ምግባር አብሮ የመስራት ችሎታ ያለው።
- የአካላዊ ብቃት (እቃዎችን የማንሳትና የፅዳት መሳሪያዎችን የመጠቀም) ችሎታ ያለው።
- ለቤተክርስቲያኗ እሴቶችና መርህሆች የሚቀበል።
ማመልከቻ አቀራረብ
ፍላጎቱ ያላችሁ አመልካቾች የሥራ ልምዳችሁን (Resume) እስከ October 25 ድረስ ማቅረብ ትችላላችሁ።
የሚቀርብበት፡ የህንፃ አስተዳደር ክፍል
ለ፡ ወንድም ኦሜጋ
የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን በቶሮንቶ
To apply for this job email your details to Omega.Demissie@eectoronto.org
