ፊልጵስዩስ 4:4-6 “ሁል ጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፤ ደግሜ እላለሁ ደስ ይበላችሁ”።
የፊልጵስዩስ ከተማ በመቄዶኒያው ንጉሥ በዳግማዊ ፊልጶስ ስም የተሰየመች ከተማ ነበረች። ፊልጵስዩስ በዘመንዋ የበለጸገች በሮም ቅኝ ግዛት ሥር የነበረች ከተማ ሲትሆን
ዘጎችዋ ከሁለቱም ከሮምና ከፊልጵስዩስ ነበሩ።
የፊልጵስዪሰ መልእክት ጠንካራ ክርስታናዊ አኗኗር የሚገልጽ ነጥቦች ያዘለ ነው፤
- ራስን ዝቅ ማድረግ (2:1-4)
- ወደ አንድ ግብ ለመድረስ ወደ ፊት መዘርጋት (3:13-14)
- ሁሉንም ለማድረግ መቻል (4:13)
- አለመጨነቅ (4:6)
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በምድር ላይ የሚኖር ሰው ሁሉ በተለይም በክርስቶስ በማመን የእግዚአብሔርን ልጅነትን ያላገኘ በአንድም ሆነ በሌላ በፍርሃት በስጋትና በጭንቀት ተይዞ ከደስታ ውጪ እራሳቸውን የሚገኙ ቁጥር ሰፍር የላቸዉም። በዚህን ጊዜ እውነተኛ ልብን የሚያሳርፍ ደስታ ከየት ሊገኝ ይችላል ቢባል ትክክለኛ ምንጩ ጌታ ኢየሲስ ክርስቶስ ብቻ ይሆናል።
የፊልጵስዩስ መልዕክት በጳውሎስ እንደ ተጻፈ የጥንቷዋ ቤ/ክ ያለማመንታት መስክራለች (1:1)። ጳውሎስ መልዕክቱን የጻፈው በእሥር ቤት ሆኖ ነው (1:13-14)።
ጳውሎስ ይህን መልዕክት ሲጽፍ ቀዳሚ አላማው የፊልጵስዩስ ሰዎች የእርሱን በሮም መታሠር ሰምተዉ (1:5, 4:10-19) ስለ ላኩለት ስጦታ ለማመስገን ነበር። ይሁን እንጂ ሐዋርያው ይህንኑ እድል በመጠቀም እነርሱ ለነበሯቸው ጥያቄዎች መልስ መስጠትና እግረ መንገዱን የሚያነሳቸው ጉዳዮች ነበሩት።
- ራሱ ስለነበረበት ሁኔታ ሲሆን (1:12-26, 4:10-19)
- የፊልጵስዩስ ምዕመናን በስደት ውስጥ፣ ጸንተው እንዲቆሙና በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ቢያልፉ እንኳ በጌታ ብቻ ደስ ሊላቸው እንደሚገባ ይመክራቸዋል (1:27-30, 4:4)።
ቅዱሳን ወገኖቼ, በዚህ ጭለማ የነገሠ በሚመስልበት ወቅትና የሰው ሁሉ ልብ ከደስታ ይልቅ በሀዘን በትካዜና በቁዘማ በተያዘበት ወቅት እውነተኛ ደስታ;
- ከሰው አይገኝም
“በሰው የሚታመን እምነቱንም በሰው የሚያደርግ የተረገመ ነውና”። - በገንዘብ ሊገኝ አይችልም
” ገንዘብን መውደድ የክፋት ሁሉ ሥር ሰለሆነ” (1ጢሞት.6:10) - ከጠቢባን አይገኝም
“የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ; የአስተዋዮችን ማስተዋል እጥላለሁ (1ቆሮ 1:19) ተብሎ ስለ ተጻፈ። - ከአዋቂዎችም አይገኝም
” የዚህች አለም መርማርስ የት አለ” ? (1ቆሮ 1:20) ስለሚል።
ቅዱሳን የጌታን ልጅነት ከነሙሉ ስልጣኑ(ዮሐ. 1:12) የተቀበልን ሁላችን በአካባቢያችን የሚሆኑትንና በወረ (News) የሚነገሩትን ከመስማት ተቆጥበን ዓይኖቻችንን ወደ ተራሮች በማንሳት (መዝ 121:1) ልባችንን በተስፋ ቃሉ በመሙላት;
- በጌታ ደስ በመሰኘት (4:4)
- ደግመን ደጋግመን በእርሱ ብቻ ደሰ በመሰኘት (4:4)
- ገርነታችንን ለሰው ሁሉ በማሳወቅ (4:5)
- ጌታ ለያንዳንዳችን እጅግ ቅርብ መሆኑን ይበልጥ እየተረዳን (4:6)
- በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችንን እያሳወቅን
- ጭንቀትን አቁመን
- አእምሮን ሁሉ በሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም
- ልባችንና አሳባችንን በክርስቶስ እናስጠብቃለን (4:7)።
ጩኸት ዋይታ ለቅሶ በሞላባትና በበዛባት አለም ውስጥ እለት በእለት ስንኖር “ሰላምን እተውላችጏለሁ: ሰላሜን እሰጣችጏለሁ” (ዮሐ 14:27) ያለንን ኢየሱስ ክርስቶስን የሙጥኝ ብለን ከእርሱ ጋር በመጣበቅ በእርሱ ብቻ ደስ እየተሰኘን በጭለማ ላለች አለም ጨውና ብርሃን በመሆን ምስክሮቹ እንድንሆን ጸጋው እንዲበዛልን ጸሎቴ ነው። እወዳችጏለሁ ተባረኩልኝ።