እግዚአብሔር መድጏኒት ነው | በፓስተር ዶ/ር አለማየሁ ጎንደሬ

እግዚአብሔር መድጏኒት ነው።
ኢሳይያስ 43:3, ሉቃስ 2:11

ኮቪድ 19 የዘመናችን አስፈሪ ወረርሽኝ በሽታ አለምን እጅግ ከማሳሰብ አልፎ ጭንቀት እንቅልፍና ሰላም ማጣትን ያስከተለ እንደሆነ የታወቀ ነው። ለዚህ ኮሮና ቫይረስ መድጏኒት ለማግኘት በአለም ያሉ ጠቢባንና የምርምር ሰዎች ሌት ተቀን ቢለፉም በቅርብ መፍትኸ የሚሰጥ አልተገኘም።

እግዚአብሔር ሰውን በራሱ መልክና ምሳሌ ከመፍጠሩ በፊት እንደ ቅድመ ዝግጅት ከፈጠራቸው ነገሮች ውስጥ:

  1. ለሰው መኖሪያ የሚሆን ምቹ ስፍራ—–መሬትን አዘጋጀ
  2. ሰው በምድር ላይ ተመግቦ በሕይወት ሊያኖረው የሚያስችሉ የምግብ አይነቶችና ለመድጏኒትነት የሚጠቅሙ ንጥረ ነገሮችን እንደ ፈጠረለት ቅዱስ መጽሐፍ ይነግረናል( ዘፍ 1:1-25)።

ለሰው ጤንነት የሚጠቅሙ ብዙ አይነት መድጏኒቶች እግዚአብሔር ከፈጠራቸው እጽዋእቶችና ማዕድናት በጠቢባን ተቀምመውና ተዘጋጅተው በጥቅም ላይ ውለዋል። ሆኖም ከሁሉ የሚበልጥ:

  1. እግዚአብሔር መድጏኒት ነው: ምትክ የማይገኝለት ለሰው ሁሉ ፍቱን መድጏኒት የሆነ እርሱ ራሱ ነው::
    በነቢዩ ኢሳይያስ ሲናገር “ከእኔ በፊት አምላክ አልተሠራም ከእኔም በጏላ አይሆንም: እኔ እኔ እግዚአብሔር ነኝ; ከእኔም ሌላም የሚያድን የለም” (ኢሳ 43:10)። “እኔ የእስራኤል ቅዱስ አምላክህ እግዚአብሔር መድጏኒትህ ነኝ (ኢሳ 43:3) ይላልና።
  2. ክርስቶስ ኢየሱስ ለሁሉ የሚሆን መድጏኒት ነው: “ዛሬ በዳዊት ከተማ መድጏኒት እርሱም ክርስቶሰ ጌታ የሆነ
    ተወልዶላችጏል” (ሉቃ ስ 2:11) “ህጻን ተወልዶልናልና ወንድ ልጅም ተሰጥቶናል: ስሙም ድንቅ መካር ጏያል
    አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል” (ኢሳ 9:6)

በጠቢባንና በተማሩ ተመራማሪዎች የሚቀመሙ መድጏኒቶች አንዱ ብቻውን ለሁሉም አይነት ወረርሽኝ ወይም ሊመጣ ላለው የበሽታ አይነት ፈውስ መስጠት አይችልም; ግን እግዚአብሔር በመጀመሪያ:

  1. ጥበቃ በማድረግ መድጏኒትነቱን ያሳይሃል
    1.1 እግዚአብሔር ይጠብቅሃል (መዝ 121:5)
    1.2 ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል: ከኮቪድ19ም ይጠብቅሃል (መዝ 121:7)
    1.3 ክፉ ወደ አንተ እንዳይቀርብ በማድረግ ይጠብቅሃል (መዝ 91:10)
    1.4 እግዚአብሔር ነፍስሕንም ይጠብቃል (መዝ 121:7)
  2. እግዚአብሔር እራሱ መድጏኒት በመሆን
    2.1 ለወደዳቸው ለእስራኤል መድጏኒትህ እኔ ነኝ እንዳላቸው ሁሉ (ኢሳ 43:3)
    2.2 ለአንተና ለመላው ቤተሰብህ ሲጋትና ጭንቀት ባስከተለብህ በኮሮና ላይ እግዚአብሔር መድጏኒትህ ነው
    2.3 ለEECT ምዕመን ሁሉ እውነተኛና ፍቱን መድጏኒት እርሱ ብቻ ነው። “ቅዱሳችሁ የእስራኤል ፈጣሪ
    ንጉሣችሁ እግዚአብሔር ነኝ።

እግዚአብሔር ከዚህ በታች ለሚከተሉት ፍቱን መድጏኒት ነው:

  1. እግዚአብሔር ለፍርሃት መድጏኒት ነው:: ከኮሮና ይልቅ ወረርሽኙ እያስከተለ ያለው ፍርሃት ሰውን በይበል እንደጎዳ በሰፋት ይኘገራል; ሆኖም እግዚአብሔር እስራኤልን
    1.1 ” ተበዥቸሃለሁና አትፍራ; እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ” (ኢሳ.43:1, 5) እስራኤልን እንደ ሕዝብ በቅዱስ ደሙ ዋጅቶአቸው የራሱ ስላደረጋቸው
    ፍርሃት እንደማይገዛቸው አጥብቆ ይነግራቸውና ጨምሮም “አንተ የእኔ ነህ” ይለዋል። እኛም በገዛ ደሙ
    ተገዝተን የእርሱ በመሆናችን ከፍርሃት ነጻ አውጥቶናል።
    1.2 ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የሞአብ የአሞንና የተራራ ሰዎች በብዙ ትጥቅ ሊወጉት በመጡበት ጊዜ እግዚአብሔርን
    በማመን ፍርሃትን አስወግዶ ከመዘምራን ጋር ወደ አምልኮ እንደገባ (2ዜና 20:17) እኛም ሁላችን በዝማሬ በምስጋና ሆነን የእግዚአብሔርን ፍት እየፈለግን “ቸር
    ነውና ምሕረቱም ለዘላለም ነውና” እያልን ፍርሃትን አስወግደን በእምነት ጸንተን ማዳኑን እንይ።
  2. በምናልፍበት ማንኛውም ሁኔታ እግዚአብሔር መድጏኒት ነው።
    2.1 እስራኤል በውጏ ውስጥ ባለፈ ጊዜ እግዚአብሔር አብሮአቸው በመሆን መድጏኒትነቱን አሳያቸው (ኢሳ 43:2)
    2.2 እግር ጠልፎ በሚጥል ወንዝ ውስጥ እስራኤል እያለፈ አይዞአችሁ አትሰጥሙም እኔ መድጏኒትህ ነኝና
    ብሎ እንዳሻገራው እኛንም የኮሮና ወረርሽኝን ክፉ ዘመን ያሻግከናል (ኢሳ 43:2)።
    2.3 እስራኤል በእሳት ውጥ ሲያልፍ እንዳይቃጠል ነበልባሉም እንዳይፈጀው እግዚአብሔር እውነተኛ መድጏኒት እንደሆናቸው ሁሉ ለእኛም ከኮሮና ቃጠሎና ፍጅት ያስመልጠናል።
  3. እግዚአብሔር በግብጽ በሽታ ላይ መድጏኒትህ ነው::
    3.1 ዘጸአት 15:26 “በግብጽ ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላደርስብህ እኔ ፈዋሽህ እግዚአብሔር ነኝ” እንዳለ
    ሁሉ ዛሬም በዘመናችን ካለው ማንኛውም አስፈሪ ከሆነ የግብጽ በሽታ መድጏኒት ሆኖ ይፈውሰናል።
    3.2 ንጉሥ ኢዮሳፍጥ የገጠመውን ጠላት ሰልፍ ለእግዚአብሔር ከተወ በጏላ “ይሁዳና ኢየሩሳሌም ሆይ ተሰለፉ ዝም ብላችሁ ቁሙ የሚሆነውን የእግዚአብሔርን መድጏኒት እዪ” (2ዜና 20:17)
    ብሎ እንዳለ እኛም በአሁኑ ጊዜ በእምነት ጸንተን በመቆም ማዳኑንና ክብሩን እንድናይ ጌታ
    ይረዳናል።

እጅግ ለተወደዳችሁ የEECT ቅዱሳን የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር; ልጁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለምደርስብን ማንኛውም ጥቃት መድጏኒታችን ስለሆነ እጅግ ደስ ይበለን ሐሴትም እናድርግ። ይህን ለአለም ሕዝቦች ሁሉ በቂ የሆነ የእግዚአብሔርን መድጏኒትነት ለሌሎች በማካፈል እንትጋ። ተባረኩ እንወድዳችጏለን።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *