እግዚአብሔር ረዳቴ ነው አልፈራም | ከፓስተር ሊንዳ

መልእክት ለወላጆች – ኮሮና ቫይረስና በቤት የተቀመጡ ልጆቻችን

ከፓስተር ሊንዳ

ግንዛቤያቸ እንደየእድሜያቸው ቢለያይም ልጆቻችን ስለኮሮና ቫይረስ ሰምተዎል። ከkG ጀምሮ ያሉት ከተቀየሩት ሁኔታዎች በተያያዘ አዲስ ክስተት መፈጠሩን ይረዳሉ።ዴይ ኬር የሚሄዱት መሄድ ባለመቻላቸው ፣ትምህርት ቤት የሚሄዱትም በመቅረታቸው፣ወደ ሱቆችና ሞሎች ፣ሪክሬሽን ሴንተርና ፕሌይ ግራውንድ እንደ ቀድሞ ባለመሄዳቸው ልጆች ከበድ ላይ ነገር እንደተፈጠረ ይረዳሉ።

የተፈጠረው አዲስ ነገር ፍርሀትና ስጋት ይፈጥርባቸዎል በዚህን ጊዜ ወላጆች ከነርሱ ጋር መሆናችንን እንደምንከልላቸው እንደምናስብላቸው እንደምንጠብቃቸው ልንነግራቸው ልናሳያቸው ያሻል።ከሁሉ በላይ ደግሞ እየሱስ ከኛ ጋራ እንደሆን ጠባቂያችን አባታችን ተንከባካቢያችን እንደሆነ እንደምንታመንበት ልንነግራቸው ያሻል።

ልጆቻችን በኛ ላይ መረጋጋትን ፅናትን በእግዚአብሔር ላይ መታመንን ሊያዩ ያስፈልጋል።በንግግር ብቻ ሳይሆን ፊታችን ላይ ባለው እርጋታ ቀስ ብለን ተረጋግተን በማውራት በእግዚአብሄር ላይ ባለን እምነት የፀናን መሆናችንን ልናሳይ ይገባል።

ልጆቻችን የራሳቸው የቤተሰባቸው የግዎደኞቻቸው ደህንነትና የወደፊት ነገራቸው ያሳስባቸዎል።ዳግም ትምህርት ቤት፣መጫወቻ ሜዳ ፣ፊልም ቤት፣ግዎደኞቻቸው ቤት መሄድ መቻል አለመቻላቸው ጥያቄና አለመረጋጋት ይፈጥርባቸዎል።

ስለኮሮና ቫይረስ እንደየ እድሜያቸው እውነቱን ልንነግራቸው ይገባል።ለትናንሾቹ ከጉንፋን ተመሳሳይ የሆነ በሽታ መሆኑን ብዙዎች ቤት ውስጥ ሆነው እንደሚሻላቸው ሀኪም ቤት ገብተውም የሚታከሙ ሊኖሩ እንደሚችሉ እንንገራቸው።ቫይረሱ የሚተላለፍበት መንገድን ስለ እጅ መታጠብ በቤት ውስጥ ተወስኖ የመቀመጥ ምክንያትና ሌሎችንም ጠቃሚ መረጃዎች እናካፍላቸው።

በቤት ውስጥ እንደ ቤተሰብ እንፀልይ ለያንዳንዱ ልጅ ደግሞ በግል እንፀልይ።ስለሁኔታው እያንዳንዱ ልጅ ያለው ምልሻ የተለያየ ስለሆነ ቤት ለምንውል ከአንድ ጊዜ በላይ አብረናቸውና በተናጥል ከያንዳንዳቸው ጋር እንፀልይ።ፀሎታችን የጥድፊያና የኛ ብቻ አይሁን።ለማን መፀለይ እንደሚፈልጉ ጠይቀናቸው እንዲፀልዩ እናርግ።ስለ አስተማሪዎቻቸው አብረዎቸው ስለሚጫወቱ ግዎደኞቻቸው መፀለይ እንደሚፈልጉ ጠይቀናቸው አዎ ካሉ እንዲፀልዩላቸው እናርግ።

በተለያዩ ቦታዎችን ሀገራት ካሉ ዘመዶችና ቤተሰቦች ጋር በስልክ በቪዲዬ በስካይፕ እንዲተያዩ እንዲነጋገሩ እናድርግ
ወደ መኝታ ከመሄዳቸው በፊት በጋራ ወደ መኝታ ከሄዱ ቦሀላ ደግሞ ለያንዳንዳቸው እንፀልይ የእየሱስና የወላጆቻቸውን አብሮነት ከነርሱ ጋራ መሆናችንን እንግለፅላቸው።

ከኮሮሮና ቫይረስ በተያያዘ ቀኑን ሙሉ ዜና ሲያዩ እንዳይውሉ እንጠንቀቅ።ሌሎች የቤተሰብ ፊልሞችን ጨወታዎችን ጊዜ ወስደን አብረን እናድርግ
መጠንና ጥልቀቱ ይለያይ እንጂ ልጆችም ፍርሀትና ስጋት አለባቸው።ሁኔታዎች እንዲህ ሲለዎወጡ ይሰጋሉ።በፊታቸው እንርበትበት አንደንግጥ በድንጋጤ ድምፅ አናውራ።እንፀልይ መፅሀፍ ቅዱስ እናንብብ እንዘምር አብረናቸው እንጫወት።ይህ ጊዜ ይበልጥ የምንቀራረብበይሁን።ለቤተሰቦችና ልጆች በቃላችሁ እንድትይዙት ይህንን ጥቅስ አተውላቹሀለሁ

ዕብራዊያን 13:6

ጌታ ረዳቴ ነው አልፈራም
እግዚአብሄር ረዳታችን ነው አንፈራም።
ፓስተር ሊንዳ
ፓስተር ሊንዳ ከዚህ በተያያዘ ከፓስተር ህዝቂያስ ማንደፍሮ ጋር ያደረጉት ውይይት ሊንክ እዚህ ታገኙታላችሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *