ማሳሰቢያ፦ ለኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን ቅዱሳን ሁላችሁ!

ተሰብስበን አንድ ላይ ማምለክ ካቆምንበት ሳምንት ጀምሮ በተገኘው አማራጭ በቴክኖሎጂ አማካይነት እየታገዝን Online የእግዚአብሔርን ቃል እየተካፈልን እንገኛለን፡፡ ወገኖችም በቴሌፎንና Skype እየተደዋወላችሁ እየጸለያችሁ እንደሆነ እናውቃለን፤ ስለዚህም ጌታ ይባርካችሁ፡፡ አሁን ያለው ነገር ቆሞ እንደገና ተገናኝተን አብረን ጌታን ለማምለክ በጣም እንናፍቃለን፡፡
ቀጥሎ ለቤተክርስቲያን መስጠት ያለብንን አሥራታችንና መባችንን በተመለከተ ከያለንበት ሁነን በታማኝነት እንድንከፍል ከዚህ በታች ያሉትን ዘዴዎች እንድትጠቀሙ እናሳስባለን፡፡

1ኛ. የባንክ ቼክ Void የሚል ከጻፋችሁበት በኋላ በcellphone ፎቶ አንስታችሁ ለኦሜጋ በ Text, Viber, Whatsapp… attachment ወይም በ e-mail መላክ ትችላላችሁ፣ ደውላችሁም ስለ ዝርዝሩ መነጋገር ትችላላችሁ፡፡

2ኛ. Void የተጻፈበት ቼክ ላይ ወይም ወደፊት ያሉትን ወራትና ቀኖች የተጻፉባቸው ቼኮች [Postdated Cheques] አዘጋጅታችሁ ከቤተ ክርስቲያን በር ጥግ ባለው የፓስታ ሳጥናችን [Mail Box] ውስጥ ማስቀመጥ ትችላላችሁ፡፡

3ኛ. ቼካችሁን [ጥሬ ገንዘብ ሳይሆን] በፓስታ ቤት በኩል ወደ ቤተ ክርስቲያን አድራሻ መላክ ትችላላችሁ፡፡

4ኛ. ወንድም ኦሜጋ ጋር ደውሉና በቀጠሮ ተገናኝታችሁ በCash ወይም በ Debit ካርድ ወይም በ Cheque መክፈል ትችላላችሁ፡፡

5ኛ. የቤተ ክርስቲያናችንን ድረ-ገጽ [website] ከፍታችሁ ከላይ በስተቀኝ በኩል ያለውን “Donate now” የሚለውን ተጭናችሁ ሂደቱን በመከተል መክፈል ትችላላችሁ፡፡

6ኛ. ከዚህ ጋር በተያያዘ ወይም ከዚህ ውጭ የሆነ ሌላ ጥያቄ ካላችሁ መጋቢዎችን ወይም ሽማግሎችን ደውላችሁ ማነጋገር ትችላላችሁ፡፡

NOTE:
• የወንድም ኦሜጋ ስልክ ቁ. 647-708-7949 ነው፡፡
• የኢ-መይል አድራሻ፦ omegademissie@yahoo.com

የኢ.ወ.ቤ.ክ. በቶሮንቶ የፋይናንስ አገልግሎት ክፍል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *