“ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና” (ሮሜ 8፥29)
“ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል”
(ገላ. 4፥19)
“ልጁ በብዙ ወንድሞች መካከል በኵር ይሆን ዘንድ፥ አስቀድሞ ያወቃቸው የልጁን መልክ እንዲመስሉ አስቀድሞ ደግሞ ወስኖአልና” (ሮሜ 8፥29)
“ልጆቼ ሆይ፥ ክርስቶስ በእናንተ እስኪሣል ድረስ ዳግመኛ ስለ እናንተ ምጥ ይዞኛል”
(ገላ. 4፥19)
በምዕራቡ ዓለም አቆጣጠር ጥር ወር የአዲስ ዓመት መጀመሪያና የዘመን መለወጫ ነው። አይሌ ሰዎችም ካለፈው ዓመት ይበልጥ ሕይወታቸውን ለማሻሻል ልዩ ልዩ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ፤ የሚያጨሱ ከእንግዲህ ላለማጨስ፣ የሚሰክሩ ከእንግዲህ ላለመጠጣት፣ የወፈሩ ለመቅጠን፣ የሚባክኑ ሰብሰብ ለማለት ወዘተ . . .። ይህም የአዲስ ዓመት ጅማሬ ውሳኔ (New Year Resolution) ይሉታል።
ክርስቲያን አማኞችም በአንጻሩ የሚወስኑት ውሳኔ ሊኖር ይችላል። የእርስዎስ ውስኔ ምን ይሆን? ለጌታ ብዙ ጊዜ መስጠት? ብዙ ለመጸለይ? በጌታ ቤት በታማኝነት ለመመላለስ? እነዚህ ሁሉ እጅግ አስፈላጊ ቢሆኑም ከላይ በሮሜ 8፥29 እና ገላ. 4፥19 የተጻፈውን ቃል አንብበው እስኪ ያሰላስሉ። የአንድ አማኝ ውስጣዊ መለወጥ ምን ያህል ወሳኝ እንደሆነ ቅዱስ ጳውሎስ በሁለቱም መልዕክቶች ይናገራል። ይህም የእግዚአብሔር የልብ ትርታና ጳውሎስን ምጥ ያስያዘ ጉዳይ ሆኖ ይታያል። እኛም ብዙ ውሳኔዎች ሊኖሩን ቢችሉም እንኳ ይህ ውሳኔ ግን ወደር የሌለው የሕይወታችን ዋና ግብ ሊሆን ይገባል፦ የልጁን መልክ (ክርስቶስን) መምሰልና የክርስቶስ በእኛ ውስጥ መሳል – መለወጥ – Transformation!