የጥሞና ቃል ክፍል 25

 “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት”

(1ጴጥ. 5፥7)

እግዚአብሔር ሕዝቡን ያስባል፤ እግዚአብሔር ኪዳኑን ያስባል (መዝ. 106፥45)። እግዚአብሔር ቃሉን ያስባል (መዝ. 105፥8)። እግዚአብሔር እንዲያስበን ምን ማድረግ አለብን? 1ኛ. ራሳችንን ለእግዚአብሔር መስጠት 2ኛ በስፍራችን መቀመጥ፣ በስፍራችን ሆነን እግዚአብሔርን መጠበቅ። አዎን፤ እግዚአብሔር በሥፍራችን ያግኘን። 3ኛ ወደ እግዚአብሔር መጮህ አለብን። እግዚአብሔር ከአቅማችን በላይ በሆነው ሁሉ እንድፈተን አይፈቅድም። ወደ እርሱ  ስንጮህም ጣልቃ ይገባል። የቅዱሳን ጩኸት ይህ ነው፦ “አስበኝ”። ሳምሶን የጸለየው ጸሎት ይህ ነበር (መሳ. 16፥28)። ነህምያም የጸለየው ጸሎት ይህ ነበር “አምላኬ ሆይ፥ በመልካም አስበኝ” (ነህ. 13፥31)። በዚህ ቀን የእርስዎም ጸሎት ይህ ቢሆን መልካም ነው! “እግዚአብሔር ሆይ አስበኝ! ብለው ይጸልዩ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *