ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል
በያለንበት ለቅዱሳን ሁሉ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ምሕረትና ቸርነት እንድበዛላቾሁ ከልቤ እመኝላቾጏለሁ።
ያለንበተ ወቅት በብዙ ገጽታው የደርግ አገዛዝ ዘመንን ከማስታወሱም በላይ በሶስት መንገዶች ተመሳሳይነት አለው:
- ፍርሀትን በሰው ሁሉ ውስጥ በመርጨት
- የአብያተክሮስትያናትን መሰባሰብ በማሰቀረት
- ሞትን የመጨረሻ ግብ አድርጎ በማስቀመጥ
ቅዱሳን የወንጌል አማኞች ያንን ክፉ ዘመን መሻገር የቻልነው:
- በእግዚከብሔር ላይ በመደገፍ
- ሕያው ቃሉን ይዘን በመቆም
- በጾምና ጸሎት በመትጋት
- የሕይወት ምስክርነትን በመከፋፈል
- በእምነት ጸንቶ በመቆም
የደርግ ዘመን ለብዙዎቻችን ቅዱሳን ጨርሶ የማያልፍ የጭለማ ወቅት መስሎ ቢታየንም በእምነት “በጌታ ለታመን ሁላችን የጽድቅ ጸሐይ እንደሚትወጣልን” በእምነት እየተረዳን እንጠባበቅ ነበር። አስጨናቂው የጨለማውም
ወቅት አልፎ የእግዚአብሔርን ክብሩን አየን።
ት. እምባቆም 2:4 “ጻድቅ ግን በእምነት በሕይወት ይኖራል” እንደሚል ጌታ ኢየሱስም ለማርታ በሞተ በተቀበረ በበሰበሰና በሸተተ ወንድምዋ ጉዳይ ላይ እምነት ብቻ ቢኖራት የእግዚአብሔርን ክብር እንደምታይ አረጋግጦላት ነበር። እርግጠኛ ነኝ ማርታም ካለማመን ወጥታ ከጌታዋ ጋር በእምነት እንደተስማማች “አባት ሆይ ስለሰማኼኝ አመሰግናለሁ” ብሎ የእምነት ጸሎት በማቅረብ ጌታ ኢየሱስ አልአዛርን ከሞት አስነሳው። ማርታና ማርያም ሞቶ የነበረው ወንድማቸው አልአዛር ሕያው ስለሆነ የእዚአብሔርን ክብር አዩ።
- እምነት ያበረታናል (ሮሜ 4:21)
- እምነት ለአብርሃም እንደሆነለት ጽድቅ ሆኖ እንድቆጠርልን ያደርጋል (ሮሜ 4:25)
- እምነት ተራራችንን ከፊታችን ያፈርሳል (ማርቆስ 11:23)
- እምነት የጸለየነውን እንዲሆንልን ያደርጋል (ማርቆስ 11:25)
- እምነት ሁልን ቻዮች ያደርገናል (ማርቆስ 9:23)
- እምነት በሕይወት እንድንኖር ያደርጋል (እምባቆም 2:4)
- እምነት ከፍርሃት ነጻ ያወጣናል (ማርቆስ 5:36)
እኛም ሁላችን ልክ እንደ ማርታ ጌታ በተናገረን የተስፋ ቃል ላይ ቆመን ብናምን በርግጥ እንደ ብርሃን ልጆች ይህን ክፉ ወረርሽኝን ተሻግረን ጭለማውን ወቅት አልፈን ብርሃን በማየት ክብሩን እናያለን።
ተባረኩ እወዳችጏለሁ።