የጥሞና ቃል ክፍል 13

“ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ”

(ኢያሱ 3፥5)

             እስራኤላውያን ይርዳኖስን እንዲሻገሩ የተመረጠው ጊዜ የሚገርም ጊዜ ነበር፣ ወንዙ በጣም የሚሞላበት ወቅት! ለምን? እግዚአብሔር ዛሬም እንዲሁ ችግሮች ሲሞሉ (ሲበዙ) አልያም ብዙ ጠበቅሁት፣ ብዙ ጸለይኩበት የምንላቸው ነገሮች ሲሞሉ እንድንሻገር ያደርገናል። ሲያሻግረን ደግሞ አድርቆ እንጂ አጕድሎ አይደለም። እስራኤል ዮርዳኖስን የተሻገሩት ተከፍሎና ደርቆ እንጂ ጎድሎ አልነበረምና። እኛ የመሸብን ሰዎች ልንሆን እንችላለን። ነገር ግን ቢመሽም ጌታ ያሻግራል። ዮርዳኖስን ለመሻገር የተሰጠው ትዕዛዝ አንድ ብቻ ነበር፦ መቀደስ! ዮርዳኖስን ከመሻገራቸውበፊት ሕዝቡ እንዲቀደሱ ተነግራቸው ነበር። እግዚአብሔር በእኛ ጉዳይ ላይ እንዲሠራ ከተፈለገ መጀመሪያ ራሳችንን እንድንቀድስ ያስፈልጋል። “ትቀደሱም ዘንድ ፈልጉ፥ ያእ እርሱ ጌታን ሊያይ የሚችል የለምና” (ዕብ. 12፥14) “ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና” (1ተሰ. 4፥3)። ጌታ በሕይወታችን ሊሠራና ሊያሳየን ላሰበው የተአምራት መጀመሪያ መቀደሳችን ነው! ዛሬ እጆቻችንን፣ ጆሮአችንን፣ ዓይኖቻችንን፣ እግሮቻችንን፣ አንደበታችንን . . .ለእግዚአብሔር እንቀድስ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *