የጥሞና ቃል ክፍል 16

“በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል። ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን!”

(1ጴጥ. 5፥10)

                        በዚህ ክፍል “የጸጋ ሁሉ አምላክ” የሚለውን አስተውል። እንዲሁም “በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ” የሚለውን በማስተዋል አሰላስለው። ጌታ ሲጠራን በምናልፍበት ነገር ሁሉ የሚረዳን ጸጋ፣ የሚያቆመን ጸጋ፣ የሚያሻግረን ጸጋ ይሰጠናል። ዛሬ በምን ሁኔታ ነው ያለኸው? ለምን ትፈራለህ? ይህ እንዴት አልፈዋለሁ? እያልህስ ለምን ትጨነቃለህ? “ያዕቆብ ሆይ፥ እስራኤልም ሆይ። መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ አልፋለች ለምን ትላለህ? ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ? አላወቅህምን? አልሰማህምን? እግዚአብሔር የዘላለም አምላክ፥ የምድርም ዳርቻ ፈጣሪ ነው አይደክምም፥ አይታክትም፥ ማስተዋሉም አይመረመርም። ለደካማ ኃይልን ይሰጣል፥ ጕልበት ለሌለውም ብርታትን ይጨምራል። ብላቴኖች ይደክማሉ ይታክቱማል፥ ጐበዛዝቱም ፈጽሞ ይወድቃሉ። እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም ይሄዳሉ፥ አይደክሙም” (ኢሳ. 40፥27-31) አስተውል! አምላካችን “የጸጋ ሁሉ አምላክ ነው!” የጠራህም በክርስቶስ ኢየሱስ ወደዘላለም ክብር ነው! አይደክምም! አይታክትም! ተነሥና አመስግነው! አምልከው!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *