የጥሞና ቃል ክፍል 27

“አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው”

(ኢሳ. 63፥16)

“አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ!”

(ማቴ. 23፥9)

በምዕራቡ ዓለም ባህል በየዓመቱ የሚከበር “የአባቶች ቀን” የሚባል ዕለት አለ። በዚህ ጊዜ ልጆች ልዩ ልዩ ስጦታ ለአባታቸው በመስጠት ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ዕለት ነው። ሆኖም በዚህ ቀን ጥሩ ስሜት የማይሰማቸው ሰዎችም አሉ። አባታቸውን በልጅነት በሞት ያጡ፣ ወይም ግድ-የለሽ አባት የነበራቸው፣ ወይም ጠባየ-ብልሹ አባት የነበራቸውና ባስታወሱት ቍጥር ውስጣቸው የስሜ ቍስል የሚረብሻቸው ሰዎች ጥቂት አይደሉም። ነገር ግን ምድራዊ አባት ላለንም ሆነ ለሌለን ሁሉ እግዚአብሔር አባታችን ይሆን ዘንድ ፈቅዷል። በክርስቶስ ካመንን የእግዚአብሔር አባትነት ለሁላችን የተሰጠ አስደናቂ ስጦታ ነው። በክርስቶስ ኢየሱስ አምነን አባትነቱን ከተቀበልነው ለሁላችን አባት ሊሆን ፈቅዷል። ክርስቶስን በማመንና በመንፈስ ቅዱስ ለመመራት ፈቃደኞች ለሆኑ አባት ነውና ስለሆነም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደቀ መዛሙርቱ ሲጸልዩ አባታችን ሆይ! ብለው ወደ እግዚአብሔር እንዲጸልዩ አስተምሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *