እግዚአብሔር ጋሻህ ነው | ፖስተር ዶ/ር አለማየሁ ጎንደሬ

እግዚአብሔር ጋሻህ ነው።—–ዘፍጥረት 15:1
እግዚአብሔር የጽድቅ ጋሻ ነው (መዝ 7:10)
ጋሻ ማለት መከለያ፣ መሸሸጊያ፣ መደበቂያ፣ መከላከያ፣ ማሰመለጪያ ሊባል ይችላል።

በኢትዮጵያ ሕዝቦች ታርክ ከተለያዩ ቁሳቁስ ተሠርተው ለተለያዩ ጥቅማ ጥቅም የሚውሉ ጋሻዎች አሉ። ለምሳሌ በአገር ቤት የፈረስ ጉግሥ ጫወታ ላይ ከፊት የሚሮጠው ፈረሰኛው ከጏላው ከሚወረወርበት ፈረሰኛ ፍላጻ እራሱን የሚከላከልበት ትንሽቷ ጋሻ ትባላለች።

ጥንት አብዛኛው ሰዎች ጋሻን የሚጠቀሙት ለጦር ሜዳ ውጊያ ነው። ሐዋርያው ጳውሎስ ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ሲያስተምር ከእግዚአብሔር የጦር እቃዎች አንዱ የእምነት ጋሻ እንድናነሳ አዞአል(ኤፌ.6:17) ። ጳውሎስ ምሳሌ የወሰደው በዘመኑ ከነበሩት የሮማውያን ወታደሮች ትጥቅ እንደነበረ ከታሪክ እናገኛለን። አንድ የሮማ ወታደር በጦር ሜዳ ሲዋጋ ከጠላት ከሚወነጨፍበት ፍላጻ እራሱን ለመከላከል በቁመቱ በተሠራለት ጋሻ ነበር። በጦርነት የተማረከበትን የወንድሙን ልጅ ሎጥን ለመታደግ አብርሃም በቤቱ አሳድጎ ያሰለጠናቸውን ባርያዎቹን ይዞ ለውጊያ እንደዘመተ ቅዱሰ መጽሐፍ ይናገራል
ዘፍጥረት 14:12 ። በጦርነቱም አሸነፎ የተማረኩትን ሎጥንና ቤተሰቡን ታደጋቸው።

ይመስለኛል በዚያ ጦርነት በጨበታ ውጊያ ውስጥ ስላለፈ አብርሃም ከሞት የተረፈው ለጥቂት እንደነበረ (near miss) መገመት ይቻላል።
አብርሃም ከጦርቱ በአሸናፍነት ቢመለስም ውስጡ በፍርሃት ተይዞ እንደነበረ የተመለከተ እግዚአብሔር በራእይ ተገልጦለትና

  1. “አብርሃም ሆይ አትፍራ
  2. እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ
  3. ታላቅ ዋጋህም እኔው ነኝ” አለው

በ1977 የኢትዮጵያና የሱማሌ ጦርነት እንደነበረ አንዳንዶቻችን እናስታውሳለን። ሱማሌ በሕዝብ ብዛት ከኢትዮጵያ ያነሰች ቢትሆንም በሶቭየት ህብረት የጦር መሣርያ እስከ አፍንጫዋ ከመታጠቅዋ የተነሳ የልብ ልብ ተሰምቷት the greater Somali የሚል ህልሟን ለመተግበር እስከ ድረደዋ ዘልቃ መጥታ ነበር። ኢትዮጵያም ሶማሌ ሐረርን እንዳትይዝ በካረማራ ድሬደዋንም እንዳታጠቃ በስተምስራቅ ለአየር ማረፊያ ትንሽ ስቀራት ተጠግታ ሳለች በጏይለኛ ውጊያና ጦርነት ተገታች። ተዋጊ አውሮፕላኖችን ከሚያበሩት አንድ አማኝ የሆነ ወንድማችን ለመብር ተራውን እየተጠባበቀ ሳለ ድረደዋ ከተማ በጸሎት ይተጉ ወደነበሩት ወገኖች ስልክ ይደውላል። ስልኩን ያነሳችው በነርስ ሙያ የሚታገለግል እህት ነበረች የጌታን ሰላምታ ከተለዋጡ በጏላ ያች እህት ለተዋጊው በራሪ ወንድም ዘፍ.15:1 አንብብ ብላ ትሰጠዋለች። ያም ወንድም ከግማሽ ሰአት በጏላ ተራው ደርሶት ከሌሎች ጋር ወደ ጦር ሜዳ ተሠማሩ። የመጀመሪያውን የጠላት እላማ ከአየር ወደ ምድር በመተኮስ መምታ እንደጀመሩ ከጠላት ከሱማሌ ወገን ጸረ አውሮፕላን ሮኬቶች በተዋጊ አውሮፕላኖች ላይ ተለቀቀ። አንዱ አውሮፕላን ወድያው በጸረ አውሮፕላኑ ሲመታ አማኙ ወንድም የሚያበረው አውሮፕላን አልተመታም። ለምን ? ቢባል እግዚአብሔር ጋሻህ ነው የሚለውን ቃል ይዞ ስለወጣ ነበር። ዛሬም ልክ እንደ አብርሃም ከኮረና ቫይረስ ጋር ፊትለፊት በጨበጣ ውጊያ ላይ እደመሆናችን

  1. እግዚአብሔር ብቻ ጋሻቢኖሩው:
    1.1 ከዚህ ጦርነት በአዋቂዎች ምክር መሸፈን አንችልም;
    1.2 በዘመድ በወገን ብዛት ሽፋን መከለልም አንችልም;
    1.3 የሀብትና የገንዘብ ብዛትም ከዚህ አስፈሪ ጥቃት አያሰመልጠንም
    1.4 ነገር ግን ለአለም ሁሉ ፍቱን መድጏኒት የሆነ ምትክ የለሌውና የታመነው የአብርሃም አምላክ ለሁላችን እውነተኛ ጋሻ በመሆን ያድነናል ይታደገናልም።
  2. ሰንታመንበት እግዚአብሔር ዋጋችን ነው
    2.1 ኮሮና ቫይረስ በአለም እያደረሰ ካለው አሰደንጋጭና አስፈሪ ሁነታ የተነሳ እኔስ ምን ዋጋ አለኝ ማለት ላይ የደረሱ ወገኖች ቢኖሩ
    2.2 የታመነው አምላካችን እግዚአብሔር ልክ ለአብርሃም እንዳበሰረለት “ዋጋህ/ሽ እኔ ነኝ ይለናል
  3. እግዚአብሔር ከፍርሃትም ይጋርደናል
    3.1 ከወረርሽኙ ይልቅ እርሱ በሰዎች ላይ እያደረሰ ያለው ፍርሃት ስጋትና ጭንቀት የባሰ ጉዳት እያስከተለ ስለሆነ
    3.2 እግዚአብሔር ስምህን\ሽን ጠርቶ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ ይልሃል
    3.3 እመን ብቻ እንጂ አትፍራ (ያእቆብ
    5:36) በተጨማሪ የእግዚአብሔር ጋሻነቱ በምን በምን ላይ ነው ?
  4. ለነፍሳችን ጋሻዋ ነው——-መዝ 121:7 “እግዚአብሔር ነፍስህንም ይጠብቃታል”
  5. ክፉ (ሰይጣን) ጨርሶ እንዳያአኝህ ጋሻ ነው “እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል” መዝ 121:7
  6. እግዚአብሔር ለቤተሰብ ጋሻ ነው (መዝ 121:8)
  7. እግዚአብሔር ለአገር ጋሻ ነው (ኤርም 30:7-8)
  8. እግዚአብሔር ለቤ/ክ ጋሻዋ ነው (መዝ 121:3)
  9. እግዚአብሔር ለመላው የአለም ሕዝብ ጋሻ ነው

ወገኖቼ ይህ እጅግ የሚደነቅ ጌታችንና አምላካችን እግዚአብሔር ከምሕረቱ የተነሳ በማያልቀው ርኅራሄው ከክፉ ሁሉ ጋሻችን ሆኖ ጠብቆ ያሻግረናል። በግል ሕይወቴ እግዚአብሔር ጋሻ ሆኖኝ ስንቱን መቅሰፍጥ ያሻገረኝ ሕያው ምስክር ነኝና በዚህ በሚታመን የአብርሃም አምላክ በመደገፍ በጽኑ እምነት እንታመንበትና የኮሮናን ዘመን በእርግጠኝነት በድል ያሻግረናለ። ክብር ለስሙ ይሁንለት። “ድል በድል እንሄዳለን” የሚለውን ከቻልን በግል በቤተሰብ እንዘምር። እወዳችጏለሁ ተባረኩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *