እግዚአብሔር መልካም ነው | በፓስተር ዶ/ር አለማየሁ ጎንደሬ

በክፉ ቀንም መሸሸጊያ ነው; በእርሱም የሚታመኑትን ያውቃል (ናሆም 1:7)

ወገናች ከሁሉ በፊት የጌታ ኢየሱስ ቸርነት ምሕረትና በጎነት በያላችሁበት እንዲያገኛችሁ ጸሎቴና ምኞቴም ነው። አሁን እያለፍንበት ባለው የኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅት እግዚአብሔር መልካም ከሆነ ለምን ይህ ሁሉ ደረሰብን ? ብለው የሚጠይቁና የሚማረሩ ብዙዎች እንደሚኖሩ ይገመታል። ይሁን እንጂ እግዚአብሔር በጅማሬም ሆነ በፊጻሜ እጅግ ሲበዛ መልካም አምላክ ነው።
ወቅቱ በ663 ዓ ቅ ክ አካባቢ የተፈጸመ ክስት ነው። ነቢዩ ናሆም ስለ ነነዌ ሕዝብና ስለ ይሁዳ ከጌታ እግዚአብሔር ሰምቶ የተናገረው መልእክት ነበር። የናሆም የስሙ ትርጉም መጽናናት ማለት ነው።
በ612 ዓ ቅ ክ የነነዌ ውድቀት በደጅ እንደሆነ ነቢዩ ናሆም ትንቢት ተናገረ። በ721-722 ዓ ቅ ክ በእስራኤል ሰሜናዊ ግዛት የነበረው ሕዝብ በምርኮ ተወሰደ። የእግዚአብሔር ሕዝብ የሆነውን እስራኤልን በተለይም ይሁዳን በጭቃነ ድርጊታቸው ያስቸግሯቸው ስለነበረ የነነዌ ውድቀት ለእስራኤል መጽናናትን እንዳመጣ ይነገራል። በተለይ በታላቁ የአሦር መሪ በአሰናፈር ዘመነ መንግሥት (በ669-627) ዓ ቅ ክ የነነዌ ክፋትዋ ከፍተኛ ደረጃ ደርሶ ሰለነበር ንጉሡ ከሞተ በጏላ ነነዌ እስከ ወደቀችበት (612 ዓ ቅ ክ) የነበራት ጏይልና ዝና እያሽቆለቆለ መጣ(ናሆም 1:14-2:1)።
የዚያን ጊዜ አሳሳቢ ስጋት ፍርሃትና ጭንቀት የተሞላበት ዘመን አሁን እኛ የምንገኝበትን ወቅት ይመስላል። በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ለሚወዳቸው ሕዝቦቹ መልካም በክፉ ቀን መሸሸጊያ እንደሆናቸው እንደዚሁ የደሙ ፍሬዎች ለሆን ለእኛም ለሁላችን መልካም ሆኖልናል። በዚህ በኮቪድ 19 ወረሽኝ ክፉ ወቀት

  1. እግዚአብሔር ለአለም ሕዝብ ሁሉ መልካም ነው; ጏጢአተኞችን ስለሚወዳቸው; ትእግሥተኛ ጏይሉም ታላቅ ነው (ናሆም 1:3)
    1.1 እግዚአብሔር በምሕረቱ ባለጠጋ ስለሆነ ቁጣውም እየነደደ በደለኛው መተላለፉን ተረድቶ ወደ እርሱ
    በንስሃ እንዲመለስ በቂ ጊዜ ሰጥቶት በፍቅሩ ይታገሰዋል።
    1.2 በደለኛውንም ንጹህ ነህ አይልም (1:3) ነገር ግን ለበደለኛው ያዝናል ወደ እርሱም ተመልሶ እንዲድን
    ይራራልም
    1.3 ጌታ ለዘላሌም አይጥልም አይቆጣምና ቢያዛዝንም እንደ ምሕረቱ ብዛት ይራራል (ሰቆቃወ 3:31)
  2. እግዚአብሔር ለራሱ ሕዝብ (ለቤ/ክ) መልካም ነው።
    2.1 ጌታችን ኢየሱስ እኔ መልካም እረኛ ነኝ ሌባው ሊሰርቅ ሊያርድ ሊያጠፋም ይመጣል (ዮሐንስ 10:11)። ኢየሱስ ግን ሕይወትን ከነትርፉ ሊሰጠን መጣ
    2.2 እግዝአብሔር መልካምነቱን ሁሉ በልጆቹ ፊት ያሳልፋል (ዘጸአት33:19) አሁን ኮቪድ 19 በአለም ሁሉ ስጋትና ብዙ ጭንቀት ፈጥሮ እያለም መልካምነቱ የበዛልን ብዙዎች ነን
    2.3 በክፉ ቀንም እግዚአብሔር ልጆቹ ለሆን ለሁላችን መሸሸጊያም ነው (ናሆም 1:7) አሁን ደጉ አምላካችን ጌታ ኢየሱስ ለቅዱሳን ሁላችን ከኮሮና መደበቂያ መከለያከያና ጋሻ ሆኖናል ክብር ልእልና ለስሙ ይሁን
  3. እግዚአብሔር ለቤተሰብም መልካም ነው
    3.1 ቤተሰብ እግዚአብሔር አሰቀድሞ ለክብሩ የመሠረተው አንጋፋ ተቋም ነው
    3.2 የኮሮና መመጣት ክፉ ገጽታው የበዛ ቢሆንም ለቤተሰብ ትልቅ opportunity እንደፈጠረልን
    እገምታለሁ። ከኮሮና በፊት እንደ ቤተሰብ ኑሮአችን የሩጫ ነበር ከዚህም የተነሳ በቂ ጊዜ ለልጆቻችን
    አልነበረንም። በተለይም በልጆቻችን የትምሕርት ሕይወት ተሳትፎአችን አመርቂ እንዳልነበረም
    ግምት ማስቀመጥ ይቻላል። ይህ ጊዜ እንደ ወላጆች የልጆቻችሁን skill ለይታችሁ የምታውቁበት
    ወቅት ከመሆኑም በላይ የህልማቸውን አቅጣቻ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር አብራችሁ የምታቀርቡበት እንደምሆን ተሰፋ አደርጋለሁ። ወላጆች አባትና እናትና አንድ ልብ አንድ መንፈስ ሆኖላችሁ የ Team Leadership ፈጥራችሁ ለልጆቻችሁ ጥሩ ምሳሌ በመሆን በሁሉ ነገር አይኖቻቸውን ወደ ክርስቶስ ለማድረግ እንዲችሉ ምክንት ለመሆን ጸጋው ይፍሰስላችሁ።
  4. እግዚአብሔር ለአገርም መልካም ነው
    4.1 ለኢትዮጵያ መልካም ነው
    4.2 ለካናዳ መልካም ነው
    4.3 ለሁለቱም አብዝተን መጸለይ አለብን
  5. እግዚአብሔር በእርሱ የሚታመኑት ያውቃቸዋል (1:7)
    5.1 የEECT ቅዱሳን በአምለሰካችሁ በሙሉ ጏይላችሁ እንደ ታመናችሁበት ያውቃል።
    5.2 በእርሱ እንደት እንደ ተደገፋችሁበት ማወቅ ብቻም ሳይሆን በዓይኑም ያያል።

ወገኖች ሆይ በአለማችን ብዙ አስከፊ ዘመናት በወረርሽኝም ሆነ በክፉዎች የነገሥታት አገዛዝ አልፈዋል። ከላይ ለማየት እንደ ሞከርነው በ663 ዓ ቅ ክ የተፈጸመው የአሦራውያን ክፋት የተሞላበት አገዛዝ እኛ አሁን ከምንገኝበት የከፋ የኮሮና ወረርሽኝ ወቅት ጋር እጅጉን ተመሳሳይነት አለው። ዘመን የማይሽረው ጊዜ የማይለውጠው ድንቅ ሠሪ አምላካችን ከብዙ ምሕረቱና ቸርነቱ የተነሳ ማንነቱ ስላልተለወጠ መልካምነቱ ስለ ተትረፍረፈልን ምስጋና ክብር ቅድስና ከታላቅነትና ገናናነት ጋር ሊቀበል ይገባዋል። በያለንበት ወገባችንን ታጥቀን በጌታና በጏይሉ ችሎት የበረታን እንሁን ይህም አልፎ ለልዩ አምልኮና ምስጋና እንገናኛለን። ተባረኩ እወዳችጏለሁ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *