ኢየሱስ ቤቱን ያጸዳል! | ፖስተር ዶ/ር አለማየሁ ጎንደሬ

“ኢየሱስ ወደ መቅደሰ ገባና በመቅደሱ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አወጣ: የገንዘብ ለዋጮችንም ወንበሮች ገለበጠና ቤቴ የጸሎት ቤት ተብሎ ተጽፎአል: እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችጏት አላቸው”።

ማቴዎስ 21:12-13

እሁድ ጌታችን ኢየሱስ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጫይቱ ላይ ተቀምጦ ሆሣእና ለዳዊት ልጅ እየተባለለት እየሩሳሌም የገባበት እለት ነበር።
ከሰኞ ጀምሮ በፋሲካ ወቅት ” የሕማም ሳምንት” ተብሎ የሚታወቀውን በዚህ ወቅት የምናስብበት ሳምንት ነው። ጌታችን በካሕናት እጅ አልፎ ከመሰጠቱ በፊት ከሰኞ ጀምሮ እያንዳንዱ ቀን በእንደት እንዳሳለፋቸው ተመዝግቦ ይገኛል። ይኸውም ሰኞ ዛሬ መቅደሱን በማጽዳት; ማክሰኞ የክርክር ጊዜ ነበር; እሮብ እረፍት; ሐሙስ ከሐዋርያቱ ጋር ለእራት አንድ እንጀራ የቆረሱበት ጊዜ ሲሆን; አርብ የመከራና የስቅለት ቀኑ እንደነበረ ብዙዎች ይስማማሉ። እኔ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰኞ ቀን ያከናወነውን “ኢየሱሰ ቤቱን ያጸዳል” በሚል ጥቅት አሳቦችን ላካፍላችሁ ወደድኩ።

  1. ቤተመቅደሱን አጸዳ። የጌታ ቤተመቅደስ የቱ ነው ወይስ ማን ነው ? እኔና እናንተ ቤተመቅደሱ ነን: 1ቆሮ 6:19-20 “ሥጋችሁ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት በእናንተ የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ እንደሆነ አታውቁምን” ?
    ጌታ ኢየሱስን እንደ ግል አዳኝ አድርገን ከተቀበልነው እለት አንስቶ ድነት አግኝተን ልጆች ከመሆን አልፈን የቅዱስ መንፈሱ ማደሪያዎች ሆነናል (ዮሐ14:25-17)። ቅዱስ ነኝና ቅዱሳን ሁኑ ተብሎ እንደተጻፈ የቅድስናው ተካፋዮች ሆነን ሕይወታችንን በጸጋው ልንመራ ይገባል። ስለሆነም በዋጋ እንደተገዛን ተረድተን በሥጋችን እግዚአብሔርን ልናከብሰር ይጠበቅብናል የራሳችሁ አይደላችሁምም ተብለናልና። ለቃሉ ታዘን አካሄዳችንን በፊቱ እያሳመርን፤
    1.1 Physically—-አካላችንን በምግብ በጽዳት በስፖርት ሙሉ ጤንነታችንን መጠበቅ።
    1.2 spiritually—-የውስጥ ሰዉነታችንን በቃሉና በጸሎት በማገልበት በጸጋው ከጏጢአት ርቀን ቁጣንና ንደትን ክፋትንም ከአፋችን ስድብንም የሚያሳፍርንም ንግግር ሁሉ እናስወግድ።
  2. ቤተክርትያንም የክርስቶስ አካል እንደመሆንዋ በመንፈስ ቅዱስ እያንዳንዳችን አንድ አካል እንሆን ዘንድ በመጨመር (1ቆሮ 12:13) ለእርሱ የተለየች አካሉ ብቻም ሳትሆን ህልውናውና ማንነቱ የምነገርባት ታላቅ ተልእኮውን አብሳሪ ድርጅት እንደመሆንዋ ከብዙ ከሚያጎድፉ ዘመናዊ (post-moernism) የስህተት ትምህርቶች እየተጠበቀች ጸንታ ለአለም የብርሃን መልእክት የሚታስተላልፍ ሊትሆን ስለሚጠበቅባት ከእያንዳዳችን ጸሎት ትጋትና ጥንካረንም ይጠይቀናል። ይህ ሳይሆን ቀርቶ ጌታ ስንፍናንና ቸልተኝነትን ቢያይብን መቅደሱን የሚያጸዳበት የራሱ የሆነ መንገድ እንደሚኖረው መዘንጋት የለብንም።
  3. ጌታ ኢየሱስ ይህንን ክፉ ኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ከአለማችን ላይ ጠራርጎ ሊያስወግ ልዩ ስልጣን አለው። ዘኁልቁ 11:23 “በውኑ የእግዚአብሔር እጅ አጭር ሆነ: ቃሌ ይፈጸም አይፈጸም እንደሆነ ታያለ ካለ በጏላ ለሙሴ 11:31 ነፋስም ከእግዚአብሔር ዘንድ ወጣ” የሚል ቃል ተጽፎ እናገኛለን። በዚያን ጊዜ በምድረ በዳ ሥጋ ላማራቸው የእስራኤል ልጆች ከእግዚአብሔር ዘንድ የወጣ ነፋስ የSea Food የምንለውን ከባሕር ገልብጦ በማውጣት ተአምር ሠርቶ ከመገባቸውና ካስደነቃቸው ዛሬ በግሌ የማምነው ኤልሻዳይ የሆነ አምላካችን በተመሳሳይ በታላቅ ችሎታውና ጏይሉ ከራሱ ዘንድ በሚያወጣ ብርቱ ነፉስ ኮቪድ 19 ኝን ከአለም ላይ እንዲያስወግድ እንጸልይ። ኃያሉ እግዚአብሔር የኤርትራን ባሕር ከፍሎ ሕዝቡን በደረቅ መረት ማሻገር ከቻለ: በኤልያስ ዘመንም በቀርሜልዎስ ተራራ እግዚአብሔር በፊቱ በማለፉ “ትልቅና ብርቱ ነፋስ ተራሮችን ከሰነጠቀ አለቶችን ከሰባበረ: ጌታችን ኢየሱስ የነፋሳትና የማእበል አዛዠ ከተባለ ይህ ክፉ ወረርሽኝ ለእርሱ ምኑ ነው ? ጌታችን መቅደሱን ብቻም ሳይሆን እንደቤ/ክ ጸልየን ብናምን ኮቪድ 19 ኝንም ጠራርጎ ከአለም ላይ ማጽዳት ይችላል።

ይህ አስጨናቂ ወቅት በቶሎ አልፎ ላያችሁ እናፍቃለሁ። ኢየሱስ ጌታ ነው ተባረኩ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *