eectoronto

በጸሎት የተጉ | ክፍል 5

“ከሰማይም በታች ካሉ ሕዝብ ሁሉ በጸሎት የተጉ አይሁድ በኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር” በሚል ርእስ ዘወትር አርብ የምንማረው ትምህርት አምስተኛው ክፍል. Friday May 24, 2019 — Send in a voice message: https://anchor.fm/guzoradio/message

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 40

“እኔ ላደርገው የሰጠኸኝን ሥራ ፈጽሜ በምድር አከበርሁህ” (ዮሐ. 17፥4) ይህንን ቃል ሳነበው እጅግ አስገረመኝ። ጌታ ኢየሱስ በአገልግሎቱ ሁለት ነገሮችን እንዳደረገ ያሳያል። 1ኛ እግዚአብሔር አብ የሰጠውን ሥራ “ፈጸምኩ” ይላል። 2ኛው “አከበርኩህ” ይላል። በሕይወታችን ዘመን እግዚአብሔር የሰጠን ሥራዎች አሉ። በእርግጥ ደህንነታችን የተመሠረተው መንፈሳዊ ሥራን በመሥራት አይደለም፣ ሰው የሚድነው በእምነት በጸጋው ነውና። ይህም ደኅንነታችን በእኛ ሥራ ሳይሆን ኢየሱስ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 39

“በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል” (1ጴጥ. 5፥10) በዚህ ቃል ውስጥ እግዚአብሔር ወደ ዘላለም ክብሩ እንደጠራን፣ የዚህ የመጠራታችን ዋና መሠረትም ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ እንመለከታለን። ሌላው እውነት ደግሞ ወደ ዘላለም ክብር የተጠራን ሆነን ሳለ እንኳ ለጥቂት ጊዜ መከራን ልንቀበል እንደምንችል ያሳያል። ሆኖም…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 38

“ኤርምያስ ገና በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ ሳለ የእግዚአብሔር ቃል ሁለተኛ ጊዜ እንዲህ ሲል መጣለት። ስሙ እግዚአብሔር የሆነ፥ ያደረገው እግዚአብሔር፥ ያጸናውም ዘንድ የሠራው እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። ወደ እኔ ጩኽ፥ እኔም እመልስልሃለሁ አንተም የማታውቀውን ታላቅና ኃይለኛ ነገርን አሳይሃለሁ” (ኤር. 33፥1-3) በመጀመሪያ ኤርምያስ በምን ሁኔታ እንደነበረ በክፍሉ የተጠቀሰውን ማስተዋል ይኖርብናል። “በግዞት ቤት አደባባይ ታስሮ” እንደነበር እንመለከታለን። በዚያ በግዞት…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 37

የሚጠራችሁ የታመነ ነው፣ እርሱም ያደርገዋል!” ( 1ተሰ. 5፥24) ጌታ በብዙ ነገር ለኛ ታማኝ ሆኖ ይኸው እስከዛሬ ቆመናል። ከእግዚአብሔር ጋር የተራመዱ ታላላቅ የእግዚአብሔር ባርያዎችም ይህ ታማኝነቱ እጅግ እያስገረማቸውና እያስደነቃቸው አልፈዋል። የእግዚአብሔር ባርያ ሙሴ ባሕርያተ እግዚአብሔርን እንዲህ በማለት ይገልጸዋል! “እርሱ አምላክ ነው፣ ሥራውም ፍጹም ነው መንገዱም ሁሉ የቀና ነው፣ የታመነ አምላክ ክፋትም የሌለበት፣ እርሱ እውነተኛና ቅን ነው”…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 36

“ሕዝቡም የእግዚአብሔርን ቃል እየሰሙ ሲያስጠብቡት ሳሉ፥ እርሱ ራሱ በጌንሳሬጥ ባሕር ዳር ቆሞ ነበር፤ በባሕር ዳርም ቆመው የነበሩትን ሁለት ታንኳዎች አየ፤ ዓሣ አጥማጆች ግን ከእነርሱ ውስጥ ወጥተው መረቦቻቸውን ያጥቡ ነበር። ከታንኳዎቹም የስምዖን ወደ ነበረች ወደ አንዲቱ ገብቶ ከምድር ጥቂት ፈቀቅ እንዲያደርጋት ለመነው፤ በታንኳይቱም ተቀምጦ ሕዝቡን ያስተምር ነበር። ነገሩንም ከጨረሰ በኋላ፥ ስምዖንን። ወደ ጥልቁ ፈቀቅ በል መረቦቻችሁንም…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 35

“አቤቱ፥ በሕዝብም ፊት በወጣህ ጊዜ፥ በምድረ በዳም ባለፍህ ጊዜ፥ ምድር ተናወጠች፣ ከሲና አምላክ ፊት፥ ከእስራኤል አምላክ ፊት ሰማያትም አንጠበጠቡ” (መዝ. 68፥7-8) እግዚአብሔር በሕዝቡ ፊት ሲወጣ የሚሆኑ ነገሮች እንመለከታለን። በተራራ ይሁን በሸለቆ የእግዚአብሔር ሕዝብ በሚገኝበት ሁኔታ ሁሉ እግዚአብሔር ይወጣል። ለምን ይወጣል? ሕዝቡን ስለሚወድ የቃል ኪዳን ሕዝቡን እየፈለገ ይወጣል፤ እግዚአብሔር ሲወጣ፦ የእግዚአብሔር ህዝብ ድል ይጎናጸፋል፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ…

Read More

በግምባራቸው ወደቁ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው | የማለዳ ጥሞና

ሁለት ሚልዮን የሚያህል ሕዝብ በውኃ ጥም ሲያጉረመርም መሪዎች ምን ማድረግ ይቻላሉ? ምንስ ማለት ይችላሉ? የምድረ በዳ ጉዞ እምነትን የሚፈትን ጉዞ ነው፣ አማኝ የሚናወጥበትና የሚበጠርበት ጉዞ ነው። ሰው በምድረ በዳ ሲያልፍ እንኳን በመሪዎች ላይ በእግዚአብሔር በራሱም ላይ እንኳ ብዙ መናገር የሚቃጣበት ወቅት ነው። አንዴ ይህ አማረኝ፣ አንዴም ያ አማረኝ እያሰኘ በመጎምጀት፥ ነገር ግን ባለ መርካት ጉዞ…

Read More