Weekly Devotion
የጥሞና ቃል ክፍል 24
“የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው?”(መዝ. 8፥3-4) የሰው ልጆች ሁሉ ፌደራል አባት አዳም ባለመታዘዝ ኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ አንስቶ ከእግዚአብሔር የመሸሽ ዝንባሌ የሰው ሁሉ ባሕርያዊ ጠባይ ሆኗል። አዳምና ሔዋን “ከእግዚአብሔር ከአምላክ ፊት በገነት ዛፎች መካከል ተሸሸጉ” ይላል (ዘፍ. 3፥8)። እግዚአብሔር አምላክም “ጠርቶ፦…
የጥሞና ቃል ክፍል 23
“ኢዮሣፍጥም ፈራ፥ እግዚአብሔርንም ሊፈልግ ፊቱን አቀና በይሁዳም ሁሉ ጾም አወጀ” (2ዜና 20፥3) በዚህ ክፍል ኢዮሳፍጥ በሦስት ጠላት ነገሥታት መከበቡን እናያለን። የሞዓብና የአሞን ልጆች ከምዑናውያን ጋር ኢዮሣፍጥን ሊወጉ መሰለፋቸውን ለኢዮሳፍጥ ወሬ ደረሰው ይላል። ኢዮሳፍጥም ሰው ነውና እንኳን ሦስት ጠላት አንድ ጠላትም ቢሆን ቀላል አይደለምና “ፈራ” ይላል። ሌላ ሰው ይህን የመሰለ ከበባ ቢገጥመው ሲፈራ ብሎም ብዙ ሊፍጨረጨርና…
የጥሞና ቃል ክፍል 22
“እግዚአብሔር ታላቅ እንደ ሆነ፥ ጌታችንም ከአማልክት ሁሉ እንዲበልጥ አውቄአለሁና፤ በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ እግዚአብሔር የወደደውን ሁሉ አደረገ” (መዝ. 135፥5) እዚህ ላይ “አውቄአለሁ” የሚለውን የቃሉ ማሰርያ አንቀጽ ልብ እንበል። ይህ የአእምሮ እውቀት ሳይሆን በሕይወት ልምምድ የሚገኝ እውቀትን ያመለክታል። ይህም ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የግል ትውውቅ (እውቀት) የሚመለክት ነው። ከተወለድን ጀምሮ ከቤተሰብና ከአካባቢ፣ ኋላም ከትምሕርት ቤትም ከከጓደኞችም…
የጥሞና ቃል ክፍል 21
“የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ የተሰበርውንና የተዋረደውን ልብ እግዚአብሔር አይንቅም” መዝ. 51፥17 እግዚአብሔር ለክብሩ የሚጠቀምባቸው ሰዎች የተሰበሩ ሰዎች ናቸው፤ ምክንያቱ እግዚአብሔር የሚቀበለው መሥዋዕት ከተሰበረ መንፈስና ከተዋረደ ልብ ነውና። ያዕቆብ በጵንኤል ሸለቆ ሥጋዊ ብርታቱ ከተሰበረ በኋላ፣ የጭኑን ሹልዳ እግዚብሔር ነክቶት እያነከሰ መሄድ ከጀመረ በኋላ ነበር የበረከት ሰው የሆነው፤ የእግዚአብሔርም ሐሳብ በሕይወቱ የተከናወነው። ሙሴ ዓለቱን ከመታ በኋላ…
የጥሞና ቃል ክፍል 20
“በመንፈቀ ሌሊት ግን ጳውሎስና ሲላስ እየጸለዩ እግዚአብሔርን በዜማ ያመሰግኑ ነበር፥ እስረኞቹም ያደምጡአቸው ነበር። ድንገትም የወኅኒው መሠረት እስኪናወጥ ድረስ ታላቅ የምድር መንቀጥቀጥ ሆነ፤ በዚያን ጊዜም ደጆቹ ሁሉ ተከፈቱ የሁሉም እስራት ተፈታ” (ሐ.ሥ. 16፥25-26) በጨለመብን ነገር ሁሉ እግዚአብሔር ጣልቃ ሲገባ እንዲህ ይሆናል። ለመርዶክዮስ ብሎም ለእስራኤል የተዘጋጀውን የሞት ድግስ አዋጅ ንጉሡን እንቅልፍ ነሥቶ የገለበጠ አምላክ ስለ እያንዳንዳችንም ጉዳይ…
የጥሞና ቃል ክፍል 19
“እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት” ዕብ. 13፥15 ገና ልጅ እያለሁ ክረምት ት/ቤት ተዘግቶ ከነበርኩበት ከተማ ሌላ ትንሽ ከተማ ወደሚኖሩ ዘመዶች ሄጄ የገጠመኝ እስካሁን አልረሳውም። መንደሩ የተጠባበቁ ቤቶች ያሉበት ነበር። ካረፍሁበት ቤት ወዲያ ሌሊት ሌሊት በግምት በየግማሽ ሰዓት ከማቃሰት ጋር የተቀላቀለ “ተመስገን . . .ተመስገን” የሚል የአዛውንት ድምጽ ይሰማል።…
የጥሞና ቃል ክፍል 18
“እነሆ፥ እግዚአብሔር የሚገሥጸው ሰው ምስጉን ነው። ስለዚህ ሁሉን የሚችለውን የአምላክን ተግሣጽ አትናቅ። እርሱ ይሰብራል፥ ይጠግንማል ያቈስላል፥ እጆቹም ይፈውሳሉ” ኢዮብ 5፥17-18 ይህ ቃል በኢዮብ መጽሐፍ ከሚገኙ አስደናቂ እውነቶች አንዱ ነው። እርስዎ አሁን ያሉበት ሁኔታ ሰው ላያውቅ ይችላል። ከደረሰብዎትም ነገር የተነሣ “ለምን?” የሚል ብቻ ሳይሆን “መጨረሻውስ ምን ይሆን?” የሚል ሥጋት…
የጥሞና ቃል ክፍል 17
አቤንኤዘር ” . . .እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል . . .” 1 ሳሙ. 7፥12 עַד־הֵ֖נָּה (ዓድ-ሔና) የሚለው የዕብራይስጡ ቃል “እስከዚህ ድረስ” ወይም “እስከ ዛሬ/አሁን ድረስ” የሚል መንታ ትርጉም ይሰጣል። አንዱ ቦታን ሲያመለክት ሁለተኛው ደግሞ ጊዜን የሚጠቁም ነው። ታሪኩም እንዲህ ነበር፦ እስራኤል በፍልስጥኤማውያን ላይ ድልን ከተቀዳጁ በኋላ ሳሙኤል አንድ ድንጋይ ወስዶ…
የጥሞና ቃል ክፍል 16
“በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ የጸጋ ሁሉ አምላክ ለጥቂት ጊዜ መከራን ከተቀበላችሁ በኋላ ራሱ ፍጹማን ያደርጋችኋል ያጸናችሁማል ያበረታችሁማል። ለእርሱ ክብርና ኃይል እስከዘላለም ድረስ ይሁን፤ አሜን!” (1ጴጥ. 5፥10) በዚህ ክፍል “የጸጋ ሁሉ አምላክ” የሚለውን አስተውል። እንዲሁም “በክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዘላለም ክብሩ የጠራችሁ” የሚለውን…
የጥሞና ቃል ክፍል 15
“ጴጥሮስም ሁሉን ወደ ውጭ አስወጥቶ ተንበርክኮም ጸለየ፥ ወደ ሬሳውም ዘወር ብሎ። ጣቢታ ሆይ፥ ተነሺ አላት። እርስዋም ዓይኖችዋን ከፈተች ጴጥሮስንም ባየች ጊዜ ተቀመጠች። እጁንም ለእርስዋ ሰጥቶ አስነሣት፤ ቅዱሳንንና መበለቶችንም ጠራ ሕያውም ሆና በፊታቸው አቆማት” (ሐ.ሥ. 9፥40-41) ዛሬ የሞተብህ ነገር አለ? የሞተብሽ ነገር ምንድነው? ምንም መፍቲሄ ሊሰጡ ከማይችሉ ሰዎች ተቀምጠህ ሬሳን እያየህ ይሆናል። ሬሳን በፊትህ አኑረህ እያለቀስህ…