የጥሞና ቃል ክፍል 14

“ኢያሱም ካህናቱን፦ የቃል ኪዳኑን ታቦት ተሸክማችሁ በሕዝቡ ፊት እለፉ ብሎ ተናገራቸው የቃል ኪዳኑንም ታቦት ተሸክመው በሕዝቡ ፊት አለፉ” (ኢያሱ 3፥6) እስራኤል ዮርዳኖስን ለመሻገር ታቦቱን ማስቀደም ነበረባቸው። እግዚአብሔር ይህንን ትዕዛዝ ለካህናቱ የሰጠውም ታቦቱ የእግዚአብሔር አብሮነት ተምሳሌት ስለ ነበር ነው። ሌላው ታቦቱ ከፊት እንዲመራቸው የሆነው ሃሳባቸው፣ ትኵረታቸውና አመለካከታቸው ወደ አምላካቸው እንዲሆን ነበር። ታቦቱን መከተልም በአዲስ መንገድ የመሄድ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 13

“ነገ እግዚአብሔር በመካከላችሁ ድንቅ ነገር ያደርጋልና ተቀደሱ” (ኢያሱ 3፥5)              እስራኤላውያን ይርዳኖስን እንዲሻገሩ የተመረጠው ጊዜ የሚገርም ጊዜ ነበር፣ ወንዙ በጣም የሚሞላበት ወቅት! ለምን? እግዚአብሔር ዛሬም እንዲሁ ችግሮች ሲሞሉ (ሲበዙ) አልያም ብዙ ጠበቅሁት፣ ብዙ ጸለይኩበት የምንላቸው ነገሮች ሲሞሉ እንድንሻገር ያደርገናል። ሲያሻግረን ደግሞ አድርቆ እንጂ አጕድሎ አይደለም። እስራኤል ዮርዳኖስን የተሻገሩት ተከፍሎና ደርቆ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 12

ከሰጢም ተነሱ፣ ዮርዳኖስን ተሻገሩ፣ ተስፋውን ውረሱ” (ኢያሱ 3)             እስራኤል ዮርዳኖስን ሳይሻገሩ በሰጢም ብዙ ጊዜ ቆይተዋል። በቆይታቸው ጊዜም ብዙ ነገር ደርሶባቸዋል። ለምሳሌ ከሌሎች ጋር ተደባለቁ፣ የሌሎችን ባህል በመሃከላቸው አስገቡ፤ ተስፋቸውን ጣሉ (ተዉ)፣ ብዙ ኀሳረ-መከራን አዩ። እኛም ዛሬ እንዲሁ፣ ተስፋችን አርጅቶ፣ የመከራ ጊዜአችንም ረዝሞ ሊሆን ይችላል። እግዚአብሔር ግን የገባውን ተስፋ ይፈጽማል…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 11

 “እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም ይሄዳሉ፥ አይደክሙም” (ኢሳ. 40፥31) (ከቍ. 23 – 31 ያለውን አንብብ) ሰይጣን ሰዎችን ለማጥቃት ከሚጠቀምባቸው መሣርያዎች አንዱ ተስፋ ማስቆረጥ ነው። ተስፋ ስንቆርጥ ጸልየንም ሆነ ጮኸን እግዚአብሔር የሚሰማን አይመስለንም። እንባቆም ባካባቢው ከነበረው ሥርዓት አልባነትና ቀውስ የተነሣ ተስፋ ቆርጦ ነበርና “አቤቱ፥ እኔ ስጮኽ የማትሰማው እስከ መቼ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 10

“ለበረከትም ሁን! You Shall Be a Blessing!” ዘፍ. 12፣2 በ1998 ዓ.ም. ግንቦት ወር ውስጥ Rev. Ruddy Wiebe ከተባሉት የመጽሐፍ ቅዱስ ኮሌጅ ፕሪንሲፓልና ሌሎች 6 ከተለያዩ አገሮች የመጡ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ጋር ፔንሲልቫንያና ኒውዮርክ ለአንድ ሳምንት በመዘዋወር በተለያዩ የአሜሪካ አብያተ ክርስቲያን የማገልገልና የመገልገል ዕድል ገጥሞን ነበር። በወቅቱ በተለያዩ ቦታዎች ብዙ አገልግለናል፣ ተባርከናልም። ወደ ቶሮንቶ ከመመለሳችን በፊት…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 9

የዳዊት ጸሎት ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት  “ቅዱስ መንፈስህም በጽድቅ መንገድ ይምራኝ!” መዝ. (143፡10) በዚሁ ክፍል ዳዊት የጸለየው የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማወቅ ብቻ ሳይሆን ለማድረግ ነው። እግዚአብሔር ፈቃዱን ለቅዱሳኑ ቢያንስ በሦስት ዋና ዋና መንገዶች ይገጻል። 1ኛ. በቃሉ፣ 2ኛ. በመንፈሱና 3ኛ. በሁነታዎች። ቅዱስ ዳዊትን ብቻ ሳይሆን እኛንም በከበረው የልጁ ደም የተዋጀን ልጆቹ ስለሆንን ዛሬም በመንፈሱ ይመራናል (ሮሜ 8)። ስለሆነም…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 8

“ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፤ የሚሰማውን ሁሉ ይናገራል እንጂ ከራሱ አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል” ዮሐ. 16፥13 የመንፈስ ቅዱስ ምሪት፡-  የተለወጠ ሕይወት እንዲኖረን ያደርጋል፣ ማለትም የአሮጌው ሰው ባሕርያችንን (ዝሙት፣ ርኵሰት፣ መዳራት…) ከሕይወታችን እያስወገደ በመንፈስ ፍሬ ይተካዋል። ስለሆነም ኃጢአትን አሸንፈን በድል ሕይወት እንድንመላለስ ያደርገናል። በውስጣችን የእግዚአብሔር ፍቅር ስለሚፈስ የፍቅር ሕይወት እንዲኖረን፣ በፍቅርም እንድንመላለስ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 7

በመንፈስ ተመላለሱ! (πνεύματι περιπατειτε) ገላ. 5፡16 በጥንታዊው የግሪክ ቋንቋ (Coine Greek) “ፔሪፓቴኦ” የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ውስጥ 95 ጊዜ ተጽፎ እናገኘዋለን። ትርጉሙም መሄድ፣ መመላለስ፣ መኖር፣ ራስን መግራት ማለት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ 5፣16 ላይ “πνεύματι περιπατειτε ኒዩማቲ ፔሪፓተይተ” “በመንፈስ ተመላለሱ፣ በመንፈስ ኑሩ፣ በመንፈስ ሂዱ፣ በመንፈስ ራሳችሁን ምሩ” በሚል ቃል ለአማኞች ትልቅና መሠረታዊ ትምሕርት ያስተላልፋል፤ በኤፌሶን…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 6

ሌሊቱ ይነጋል! “ሙሴም በባሕሩ ላይ እጁን ዘረጋ፣ እግዚአብሔርም ሌሊቱን ሁሉ ጽኑ የምስራቅ ነፋስ አምጥቶ ባሕሩን አስወገደው:: ባሕሩንም አደረቀው፣ ውኃውም ተከፈለ፤ የእሥራኤልም ልጆች በባሕሩ መካከል በየብስ ገቡ፣ ውኃውም በቀኛቸውና በግራቸው እንደ ግድግዳ ሆነላቸው…ንጋትም በሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በእሳትና በደመና ዓምድ የግብጻውያንን ሠራዊት ተመለከተ…አወከ…አሠረ…ወደ ጭንቅም አስገባቸው፣ ግብጻውያንም እግዚአብሔር በግብጻውያን ላይ ይዋጋላቸዋልና ከእሥራኤል ፊት እንሽሽ አሉ” (ዘጸ. 14፣21-25) በዚህ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 5

መዝ. 8፥3-9           “የጣቶችህን ሥራ ሰማዮችን ባየሁ ጊዜ፥ ጨረቃንና ከዋክብትን አንተ የሠራሃቸውን ታስበው ዘንድ ሰው ምንድር ነው? ትጐበኘውም ዘንድ የሰው ልጅ ምንድር ነው? ከመላእክት እጅግ ጥቂት አሳነስኸው በክብርና በምስጋና ዘውድ ከለልኸው። በእጆችህም ሥራ ሁሉ ላይ ሾምኸው ሁሉን ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፥ በጎችንም ላሞችንም ሁሉ ደግሞም የምድረ በዳውን እንስሶች፥ የሰማይንም ወፎች የባሕርንም ዓሦች፥ በባሕር መንገድ የሚሄደውንም ሁሉ።…

Read More