በግምባራቸው ወደቁ የእግዚአብሔርም ክብር ተገለጠላቸው | የማለዳ ጥሞና

ሁለት ሚልዮን የሚያህል ሕዝብ በውኃ ጥም ሲያጉረመርም መሪዎች ምን ማድረግ ይቻላሉ? ምንስ ማለት ይችላሉ? የምድረ በዳ ጉዞ እምነትን የሚፈትን ጉዞ ነው፣ አማኝ የሚናወጥበትና የሚበጠርበት ጉዞ ነው። ሰው በምድረ በዳ ሲያልፍ እንኳን በመሪዎች ላይ በእግዚአብሔር በራሱም ላይ እንኳ ብዙ መናገር የሚቃጣበት ወቅት ነው። አንዴ ይህ አማረኝ፣ አንዴም ያ አማረኝ እያሰኘ በመጎምጀት፥ ነገር ግን ባለ መርካት ጉዞ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 33

“ኢያሱም ማልዶ ተነሣ፥ እርሱና የእስራኤልም ልጆች ሁሉ ከሰጢም ተነሥተው ወደ ዮርዳኖስ መጡ ሳይሻገሩም በዚያ አደሩ” ኢያሱ 3፥1 ዮርዳኖስን ለመሻገር የሚዘጋጅ ሰው ማልዶ መነሳት አለበት። ይህ ደግሞ የጸሎት ሕይወታችንን ያሳያል። የሚጸልይ ሰው ይሻገራል። የጸሎት ሰው በምንም ዓይነት መከራ ውስጥ ቢያልፍም ይሻገራል። ዳንኤል በየቀኑ ሦስት ጊዜ በአምላኩ ፊት ይጸልይ ነበር። በአድመኞች ሴራ እርሱን ለማጥፋት የተቀነባበረ አዋጅ በጽሑፍ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 32

 “ነገር ግን . . .” “የሶርያ ንጉሥ ሠራዊት አለቃ ንዕማንም እግዚአብሔር በእርሱ እጅ ለሶርያ ደኅንነትን ስለ ሰጠ በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ነበረ ደግሞም ጽኑዕ ኃያል ነበረ፥ ነገር ግን ለምጻም ነበረ” (2ነሥ. 5፥1) በእያንዳንዱ ሰው ሕይወት “ነገር ግን” የሚባል አሉታዊ የመስተጻምር ቃል አለ። ንዕማን ምንም እንኳ ታዋቂና ዝነኛ፣ ሰው “በጌታው ዘንድ ታላቅ ክቡር ሰው ….

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 31

“ኢየሱስም በቢታንያ በለምጻሙ በስምዖን ቤት ሳለ፥ አንዲት ሴት ዋጋው እጅግ የበዛ ሽቱ የሞላው የአልባስጥሮስ ብልቃጥ ይዛ ወደ እርሱ ቀረበች በማዕድም ተቀምጦ ሳለ በራሱ ላይ አፈሰሰችው። ደቀ መዛሙርቱም ይህን አይተው ተቈጡና። ይህ ጥፋት ለምንድር ነው? ይህ በብዙ ዋጋ ተሽጦ ለድሆች ሊሰጥ ይቻል ነበርና አሉ። ኢየሱስም ይህን አውቆ እንዲህ አላቸው፦ መልካም ሥራ ሠርታልኛለችና ሴቲቱንስ ስለ ምን ታደክሙአታላችሁ?…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 30

“ለክርስቶስ ወንጌል እንደሚገባ ኑሩ!” (ፊል. 1፥27-30) ክርስቶስ ሕይወት ነው፣ ሕይወትም ኑሮ ነው። ቅዱስ ጳውሎስ “ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ ሞትም ጥቅም ነው” (ፊል. 1፥21) ብሏል። ወደ ጌታ ስንመጣ ምንም ነገር ከማድረጋችን በፊት አስቀድመን ከእርሱ ጋር መኖር መለማመድ አለብን። ከአገልግሎት በፊት መኖር አስፈላጊ ነው።  ከመኖር የተነሳ የምንሰጠው አገልግሎት ፍሬ አለው። “በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 29

“ጌታም ባያት ጊዜ አዘነላትና። አታልቅሽ አላት። ቀርቦም ቃሬዛውን ነካ፥ የተሸከሙትም ቆሙ፤ አለውም። አንተ ጐበዝ፥ እልሃለሁ፥ ተነሣ። የሞተውም ቀና ብሎ ተቀመጠ ሊናገርም ጀመረ፥ ለእናቱም ሰጣት” (ሉቃስ 7፥13-17)  ጌታ ኢየሱስ በአንድ መቶ አለቃ እምነት እየተደነቀ ከቅፍርናሆም ናይን ወደምትባል ከተማ አመራ። በናይን ከተማም አንድያ ልጇ የሞተባትን ሴት አይቶ አንዳዘነላትና ልጁን ከሞት እንዳስነሳ በዚህ ክፍል ተጠቅሷል። የሞቱትን ስለ ማስነሳት…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 28

“ነገር ግን ቃል ተናገር፥ ብላቴናዬም ይፈወሳል!” (ሉቃስ 7፥7) ሉቃስ ምዕራፍ ሰባት ብዙ አስደናቂ ታሪኮችን ይዟል። የመጀምሪያው ኢየሱስ ወደ ቅፍርናሆም ሲገባ የተገለጠው የአንድ መቶ አለቃ እምነት ነበር። ይህ መቶ አለቃ የሮማውያንን መንግሥት የሚያገለግል ባለ ሥልጣን ነበር። በዚያን ጊዜ የእስራኤል ምድር ከአንድ መቶ ዓመት ዘመን በላይ በሮማውያን መንግሥት ቅኝ ግዛት ሥር ነበረች። ነገር ግን የመቶ አለቃው ጨካኙን…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 27

“አብርሃም ባያውቀን እስራኤልም ባይገነዘበን አንተ አባታችን ነህ አቤቱ፥ አንተ አባታችን ነህ፥ ስምህም ከዘላለም ታዳጊያችን ነው” (ኢሳ. 63፥16) “አባታችሁ አንዱ እርሱም የሰማዩ ነውና በምድር ላይ ማንንም አባት ብላችሁ አትጥሩ!” (ማቴ. 23፥9) በምዕራቡ ዓለም ባህል በየዓመቱ የሚከበር “የአባቶች ቀን” የሚባል ዕለት አለ። በዚህ ጊዜ ልጆች ልዩ ልዩ ስጦታ ለአባታቸው በመስጠት ፍቅራቸውን የሚገልጹበት ዕለት ነው። ሆኖም በዚህ ቀን…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 26

“ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን ለአምላክ ለመድኃኒታችን እልል እንበል” መዝ. 95፥1 ቅዱስ ዳዊት “ኑ፥ በእግዚአብሔር ደስ ይበለን!” የሚል ጥሪ አቅርቦአል። እንደ ገናም “ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ሲሉኝ ደስ አለ” ይላል። ቅዱስ ጳውሎስም “ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ፣ ደግሜ እላለሁ፥ ደስ ይበላችሁ” (ፊል. 4፥4) ይላል። ብዙ መከራና ውጣ ውረድ ባለበት ዓለም፣ በየቀኑ ተግዳሮት በበዛበት ዓለም እንዲት ብሎ ሁሌ…

Read More

የጥሞና ቃል ክፍል 25

 “እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት” (1ጴጥ. 5፥7) እግዚአብሔር ሕዝቡን ያስባል፤ እግዚአብሔር ኪዳኑን ያስባል (መዝ. 106፥45)። እግዚአብሔር ቃሉን ያስባል (መዝ. 105፥8)። እግዚአብሔር እንዲያስበን ምን ማድረግ አለብን? 1ኛ. ራሳችንን ለእግዚአብሔር መስጠት 2ኛ በስፍራችን መቀመጥ፣ በስፍራችን ሆነን እግዚአብሔርን መጠበቅ። አዎን፤ እግዚአብሔር በሥፍራችን ያግኘን። 3ኛ ወደ እግዚአብሔር መጮህ አለብን። እግዚአብሔር ከአቅማችን በላይ በሆነው ሁሉ እንድፈተን…

Read More